የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ለ4ኛ ግዜ በዶክቶሬት ድግሪና ለ10ኛ ዙር በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን 2 መቶ 87 ተማሪዎች አስመርቋል።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሐምሌ 30/2014

በምረቃ ፕሮግራም በክብር እንግድነት የተገኙት የፌዴራል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባበሪ ሚንስቴር ዶ/ር አለሙ ስሜ እንደተናገሩት የሰው ልጅ በማህበራዊም ይሁን በኢኮኖሚ ዘርፎች ዕድገትና ለውጥ ሊያስመዘግብ የሚችለው ጤና ስኖር ነው።

ተመራቂ ተማሪዎችም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀያር ህብረተሰቡን በርህራሄ በመንከባከብ እንዲያገለግሉ መልዕክታቸውን አስተላልፏል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ በምረቃ ወቅት ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው በምርምር፣ በመማር ማስተማርና ማህበረሰብ አቀፍ ተልዕኮዎች የተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።

የሰላም አምባሳደር በሆነው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ክልል ከአክሱምና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በሠለም መደፍረስ ምክንያት ከመንግስት አደራ የተቀበላቸውን በባዮቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 34 ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ 3 መቶ 21 ተማሪዎች መመረቃቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አመታት ከ27 ሺህ በላይ ምሩቃንን በተለያዩ የሙያ መስኮች አስተምሮ ለሀገር የተማረ የሰው ኃይል ልማት ማበርከቱን ዶ/ር ሀብታሙ አንስተዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታ የቀሰሙትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር በመለወጥ ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ህይወት ላይ የሚሰሩ እንደመሆናቸዉ መጠን በከፍተኛ ኃላፊነት እና በጥሩ ስነ-ምግባር ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

ከተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውም የተለያዩ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶችን አልፈው ለምረቃ መብቃታቸውን እንዳስደሰታቸው ተናግረዉ ባገኙት አጋጣሚ በጥሩ ስነ-ምግባር ለማገልገል ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል።

Share this Post