የሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶች በማፅደቅ ተጠናቋል ።በዚህም መሠረት

1ኛ አቶ ሊሩ ጀማል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

2ኛ ዶ/ር ደበበ ገብሬ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ

3ኛ አቶ ኤርሚያስ ባፋ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የኢን/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ 4ኛ አቶ አዲሴ ኢፋ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ረዳት ተጠሪ/ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላ 5ኛ አቶ ፍቅሩ መሉ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ረዳት ተጠሪ /የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል ።

አዲሱ ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማል ባደረጉት ንግግር በሆሳዕና ከተማ የሚስተዋሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታት ለወጣቱ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ህገ-ወጥ አሰራሮችን በማስተካከል ሆሳዕና የንግድና የኮንፍራንስ ማዕከል ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ በመጠቆም የምክር ቤቱ እገዛና ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል።

ዘገባ የሆ/ከ/አስ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ጥቅምት 5/2015 ዓ.ም

Share this Post