12
Aug
2022
የሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ የሥራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ጉባኤ እንደ ቀጠለ ነው።
ሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ገዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 5/2014 ዓ.ም
የምክር ቤቱ ጉባኤ በትላንትናው ዕለት የ21ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ፣የም/ቤቱ ጽ/ቤት የ2014 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀና የ2015 ዓ,ም ጠቋሚ ዕቅድ ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን የከተማው አስተዳደር የ2014 ዓ.ም ማጠቃለያ የክንው ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
የምክር ቤቱ አባላት በዛሬው ዕለት የአስፈፃሚውን አካል መነሻ በማድረግ በከተማው በመሬት አስተዳደር ፣ በአገልግሎት አሠጣጥ ፣ በገቢ አሰባሰብ ፣ በመሠረተ -ልማት ፣ በትምህርት ጥራት ፣ በህገ-ወጥ ንግድ ፣ በትራንስፖርትና በሌሎች ዘርፎች የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ላቀረቡዋቸው ጥያቄዎች በም/ከንቲባ በአቶ በየነ ሻንቆና በሚመለከታቸው የካቤኔ አካላት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል ።
የም/ቤቱ አባላት በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይታቸውን ቀጥለዋል ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ ፤እንኳን ደስ አለን !!