የሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ የሥራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2015 ዓ.ም የከተማው አስተዳደር ዕቅድ ማስፈፀሚያ 750 ሚሊየን ብር በጀት በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 6/2014 ዓ.ም

የከተማው ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዓለሙ እንደገለጹት ምክር ቤቱ ያፀደቀው በጀት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ38.8% ብልጫ አለው ።

ምክር ቤቱ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ያካሄደው ጉባኤ ከምክር ቤቱ ፣ ከአስፈፃሚና ከዳኝነት አካሉ የቀረበለትን የክንውንና የዕቅድ ሪፖርቶች ተወያይቶ አጽድቋል።

የምክር ቤቱ ጉባኤ ከዚህም በተጨማሪ የአለም ባንክ ፕሮጀክት የዕቅድና የአፈፃፅም ሪፖርት ፣ በከተማው ተሻሽሎ የቀረበው የውሃ ታሪፍና የገቢ ማሻሸያ ሰነዶች ለይ ተወያይቶ አፅድቋል ።

Share this Post