ልዩ መንገድ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሆሳዕና ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ40 ድጋፍ ለሚሹ አቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።

የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሽጉጢ በበኩላቸው የዘንድሮ የዘመን መለወጫ በዓል የህዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት የሚከበር በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው በመግለፅ በጠቅላይ ሚንስትራችን መሪነት እየተካሄደ ያለው የአብሮነት እና የመደጋገፍ ባህላችን ለማጠናከር ጥረት እንደሚደረግም ተናግረዋል ።

የልዩ መንገድ በጎአድራጎት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ሳምሶን ብርቅነህ እንደገለፀው የማህበሩ አባላት በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ተሰማርተው ባሰባሰቡት 100ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው ዶሮ፣የምግብ ዘይት፣ሽንኩርት የበዓል መዋያ ለሌላቸው ወገኖች ለማሰብ ድጋፉን መዘጋታቸውን ገልፆ ድጋፋ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

Share this Post