13
Sep
2022
የሆሳዕና ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ለዘማች ቤተሰቦችና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ 400 ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መስከረም 02/2015ዓ.ም
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ በከተማው ሴቶች አደረጃጀት አማካኝነት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ድርጅቶች በማስተባበር ከ140ሺ ብር በላይ ግምት ያለው ለእያንዳንዱ ህፃን ግማሽ ደርዘን ደብተርና አምስት እስክሪብቶ ድጋፍ ተደርጓል ።
አክለውም አንድም ህፃን በችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታው እንዳይለይ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ለ1,100 ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል ።
የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ በየነ ሻንቆ የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ዘመድኩን በየበኩላቸው ድጋፍ ላደረጉ ደርጅቶችና ግለሰቦችን በማመስገን ድጋፍ የተደረገላቸው ህፃናት ትምህርታቸውን በአግባቡ ሊከታተሉ እንደሚገባም አሳስበዋል ።