የሆሳዕና ከከተማ አስተዳደር የአመራር አካላት በከተማው የታቀደውን የ70 ቀን ዕቅድ በላቀ አፈፃፀም ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄደዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ህዳር 7/2015 ዓ.ም

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሊሬ

ጀማል በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በከተማው የታቀደው የ70 ቀን ዕቅድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይፋ ከተደረገው የሌማት ትሩፋት ጋር በማቀናጀት የኑሮ ውድነት በመቀነሰ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ደበበ ገብሬ በበኩላቸው ተልዕኮ መወጣት የአመራር ግዴታ መሆኑ በመግለጽ ተግባራት ከወትሮው በተለየ መልኩ በንቅናቄ በመፈፀምና በየሴክተሩ በየደረጃው እየገመገሙ ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አሰተያየት በከተማው የታቀደው የ70 ቀን ዕቅድ ለማሳካት ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።

Share this Post