በሆሳዕና ከተማ የሴች ዱና ቀበሌ አስተዳደር ከቀበሌ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ለ73 አቅመ ደካማ አረጋውያንና ለዘማች ቤተሰብ
የምግብ ፣የትምህርት ቁሳቁሶችና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም
የሴች ዱና ቀበሌ ዋና አስተዳደር አቶ ታምራት ከሣና በቀበሌው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጠዉ በየበኩላቸው አቅመ ደካማ አረጋዊያንና የዘማች ቤተሰብ መካከል ለተወጣጡ ተረጂዎች የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የምግብ ዱቄት ፣ አልባሳት ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ደብተር ና እስክርቢቶ በብር ግምት ከ55 ሽህ ብር ባለይ ግምት ያላቸው መሆኑን ጠቁመው መረዳዳት ባህላችን ስለሆነ ደቦ አጥቶ ጾም የሚያድር እንዳይኖር ሁለም ማህበረሰብ የበኩላቸውን አስተኦጽኦ ልወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
አክለውም ኃላፊዎቹ ለተረጂዎቹ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ዝቅተኛ ገቢያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ በዘላቂነት ራሳቸውን ለማቋቋም መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው 2015 ዘመን መለወጫ በዓል ትውልደ ኢትዮጵያውን በሙሉ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፏል ።
በመጨረሻም ተረጂዎች በሰጡት አስተያየት ከምግብና አልባሳት ቁሳቁስ በላይ ኑሮ ውድ በሆነ ወቅት ላይ ልጆቻችን ማማር እንድችሉ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።