በሆሳዕና ከተማ አራዳ ቀበሌ ለሚገኙ ለ750 ለተወጣጡ አቅመ ደካሞች ህፃናት ቤተሰብ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ እንዲሁም ለ320 ዪኒፎም ድጋፍ ተደርጓል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 20/2015 ዓ.ም

SOS ህፃናት መንደር ኢትዮጵያ ሀዋሳ ፕሮግራም አራዳ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ በላይ ይልማ እንደገለፁት የቤተሰብ እና የልማት ድርጅቱ ከዚህ በፊት ለተከታታይ ጊግዜያት የተለያዩ ድጋፎችንና የብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመገናትና በመመቻቸት ያለው መሆኑን ጠቁመዋል ።

አክለውም አስተባባሪው በችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ሳይማር መቅረት እንደሌለበት ጠቁመው ከ750 በላይ አቅመ ደካሞች ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ስሆን በተጨማሪ ከተመለመሉት ወስጥ ለ320 ህፃናት ዩኒፎርም አልባሳት ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው በአጠቃላይ 800,000 ሽ ብር በላይ ግምት ያለው መሆኑን የSOS ህፃናት መንደር ኢትዮጵያ ሐዋሳ አራዳ ፕሮጀክት ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል ።

በመጨረሻም የፕሮጀክቱ ተሳታፊ የህፃናት ቤተሰብ የሰጡት አስተያየት ኑሮ ዉድ በሆነው ጊዜ ከSOS ፕሮጀክት ድጋፍ በመገኘታችን መማር መቻላቸውን ጠቅሰው ለፕሮጀክቱን ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

Share this Post