የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበው ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የስንቅ ድጋፍ ለዞኑ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረከበ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበው ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የስንቅ ድጋፍ ለዞኑ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረከበ ።

የሆሳዕና ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ጳጉሜ 03/2014 ዓ/ም

ከከተማው ማህበረሰብ በስድስተኛ ዙር ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ከተደረጉ ድጋፎች መካከል 44 ሠንጋዎች ፣34 በግና ፍየል ፣ 32.5 ኩንታል ስኳር እና 275 ኩንታል ቆሎና በሶ ይገኙበታል ።

ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር በአንድነት እንቆማለን፣ በሉዓላዊነታችን ተደራድረን አናውቅም ታሪካችን ምስክር ነው፣ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ጎን እንቆማለን፣ የህወሃት ጁንታ ቡድን የሁሉም ኢትዮጲያዊ ጠላት ነው ።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር ህዋሓት ለ3ተኛ ጊዜ የከፈተብንን ወረራና ጦርነት ለመቀልበስና በድል ለማጠናቀቅ ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን መሆናችንን እንገልፃለን የሚሉ መፈክሮች በፕሮግራሙ ላይ በተገኙ ነዋሪዎች ተስተጋብቷል።

Share this Post