06
Oct
2022
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 21/2015 ዓ.ም
የሎቭ ኦርዴር ቸርት የበጎ አድራጎት ማህበር
አስተባባሪ አቶ ማናዬ ጴጥሮስ እንደገለፁት በችግር ምክንያት ሳይማር መቅረት እንደሌለበት በመሳብ ከ72 ሽ ብር በላይ ግምት ያለው ሀብት ማህበሩ ከወ/ሮ ብዙነሽና ቤተሰብ ጋር በመተባበር አቅመ ደካሞች ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳትን ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ወ/ሮ ስንታየሁ ምርከ በበኩላቸው መረዳዳት ባህላችን በመሆኑ ማህበሩ በራሳቸው ተነሳሽነት ለችግር የተጋለጡ ማህበረሰባችን ከለው ሀብት በመካፈል ላበረከቱት ድጋፍ በማመስገን ተረጂዎችም ከተረጂነት ወጥተው ረሳቸውን በመቻል ለሌሎች መረዳት የሚችሉበትን አቅምን ለመፍጠር ተጠናክሮ መሥራት ወሳኝ ነዉ ብላዋል ።
የተሳታፊ ህፃናት ቤተሰብ የሰጡት አስተያየት ኑሮ ዉድ በሆነው ጊዜ ልጆቻችን መማር እንዲችሉ ለተባበሩት ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።