በሆሳዕና ከተማ አራዳ ቀበሌ ለሚገኙ 90 አቅመ ደካማ ህፃናት ቤተሰቦች SOS ህፃናት መንደር ሐዋሳ ሆሳዕና አራዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከ90 ሽህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ ።

በሆሳዕና ከተማ አራዳ ቀበሌ ለሚገኙ 90 አቅመ ደካማ ህፃናት ቤተሰቦች SOS ህፃናት መንደር ሐዋሳ ሆሳዕና አራዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከ90 ሽህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ ።

የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጳጉሜ 01/2014 ዓ.ም

SOS ህፃናት መንደር ሀዋሳ ሆሳዕና አራዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ በላይ ይልማ እንደገለፁት የቤተሰብ እና የልማት ድርጅቱ ከዚህ በፊት ለተከታታይ ሁለት ዙር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው በችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ሳይማር መቅረት የለበትም ስሉ ገልፀዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ እና የአራዳ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃለፊ ወ/ሮ ብዙነሽ ብርቄ በየበኩላቸው የቤተሰብና የልማት ፕሮጀክት በተመቻቸላቸው መሠረት በመቆጠብ ከተረጂነት ተላቀው በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ረሳቸውን በመቻል ለሌሎች መረዳት የሚችሉበትን አቅም መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል ።

አክለውም ኃላፊዎቹ አሸባሪው ህወሓት ሀገርን ለማፈራረስ የከፈቱበትን ጦርነቱን በመከላከል ኢትዮጵያን የመዳን ህልውና ታንግባዉ ለሚገኙ ለጀግና መከላከያ ሠራዊት በፀሎትና አቅም በሚችለ ሁሉ የበኩላቸውን አስተኦጽኦ ልወጡ እንደሚገባም ጥሪ አቅረበዋል ።

Share this Post