49.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የ"ሆሳዕና-ጊምቢቹ-ጃቾ" የአስፖልት መንገድ ፕሮጀክት ስራ ውል ስምምነት ተፈረመ

የሆሳዕና-ጊምቢቹ-ጃቾ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ስራ ውል ስምምነት ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እና ቋራጩ መሳይ አሊ ድርጅት ፊርማቸውን አውለዋል።

የመንገዱ እርዝማኔ 49.5 ኪሎ ሜትር ሲሆን የሚጠናቀቀውም በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

በፊርማ ስምምነቱም ወቅት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የሶሮ፣ የጊምቢቹና የጃጁራ ከተማ አስተዳደር እና የምዕራብ ሶሮ ኃላፊዎች ተገኝቸዋል።

Share this Post