የ’’ያሆዴ” በዓል ዋዜማ በሆሳዕና ከተማ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው

መስከረም 13/2015ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

የሀዲያ የዘመን መለወጫ ’’ያሆዴ” በዓል ዋዜማ በሆሳዕና ከተማ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡

በዋዜማ በዓሉም በደቡቡ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የደቡብ ክልል መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ስንታየው ወ/ሚካኤል፣ የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሀ/ማሪያም የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ባህል ሽማግሌም፣ የብሔሩ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በያሆዴ በዓል ዙሪያ የተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሑፍ በመቅረብ ላይ ሲሆን በቀጣይ ውይይት ይደረግበታል፡፡

በዛሬው ዕለት በቅርቡ የስርጭት አድማሱን ወደ 24 ሰዓት ያሳደገው የሀዲያ ቴሌቪዥን የምረቃ ስነ-ስርዓት ይቃሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በይዲድያ ተስፋሁን

Share this Post