የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ የ"ያሆዴ" በዓል በዱና ወረዳ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከበረ

መስከረም 12/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ "የያሆዴ" በዓል በዱና ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በየዓመቱ በወረሃ መስከረም አጋማሽ የሚከበረው የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ "የያሆዴ" በዓል የወረዳው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የባህል ሽማግሌዎች እና የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በባዓሉ አከባበር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታምሬ የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል ሰፊ የህዝብ መሰረት ያለው መሆኑን አና በዓሉም የዕርቅ፣ የመከባበርና የማህበረሰባዊነት እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ለበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ያስተላለፉት የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ አበራ የያሆዴ በዓል በሀድያ ብሔር ከረዥም ግዜ አንስተው እየተከበረ ያለ ስሆን አሁን ላይ በሁሉም የሀድያ ህብረተሰብ ዘንድ ሰፋ ያለ የህዝብ መሰረት ይዘው እየተከበረ እንዳለ አንስተዋል። በተጨማሪም የበዓሉ ታዳሚ የሆኑ የአከባቢው የባህል ሽማግሌዎች በአከባቢው ሰላም፣ ዕድገት እና ብልፅግና እንድሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በዓሉ ሲከበር በርካታ የብሔሩ ማንነት፣ ታሪክ፣ ቋንቋ ፣ የአኗኗር ስርዓት ባህላዊ እሴቶች ጎልተው የሚፀባረቁበት ነው፡፡ በዓሉ የእርስ በርስ ግንኙነት የሚያጠናክር አንድነትን በይበልጥ የሚያጎለብት በመሆኑ ህዝባዊ መሰረት ኖሮት ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ በውስጡ አካትቶ የያዘቸው የመቻቻል፣ የአብሮነትና የአንድነት እሴቶች ትስስርን በማጠናከር በይበልጥ ማጎልበት ይገባል በማለት አንስተዋል ።

ዘገባው፦ የዱና ወ/ብ/ፓ/ን/ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ህዝብ ግንኙነትነው።

Share this Post