14
Nov
2022
ህዳር 3/2015ዓ.ም
በስልጠናው ላይ ከየቀበሌው የተወጣጡ ሴቶች ፣የመሰረታዊ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣የዕድሮች ጥምረት አባላትና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ቲርካሶ ባደረጉት ንግግር ህብረተሰቡ ከህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውና ከህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ሰቆቃን እንጂ መቼም ስኬትን ማሰብ እንደማይቻል በመገንዘብ የዚህን እኩይ ተግባር ፈፃሚዎች በማጋለጥና በማስተማር በየአደረጃጀቱ በጎ ተጽዕኖ በመፍጠር ችግሩ ለመቀነስ በጋራ መስራት እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል ።
አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የዕድር መሪዎች ፣የሀይማኖት አባቶችና ተዋቂ የሀገር ሽማግሌዎች አቅም ደካሞችን በመርዳት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ለማስቆም የሚያስችል ደንብ በማውጣት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል ።