የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በልዩ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉ የሀድያ ዞን ወጣቶች ፌደሬሽን ገለፀ
የሀዲያ ዞን ወጣት አደረጃጀቶች ከፎንቆ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን የተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትን በፎንቆ ከተማ አከናወኑ።
የሀድያ ዞን የመ/ኮ/ጉ/መ (5/12/2014 ዓ.ም)
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መረሃ-ግብር ላይ የሀዲያ ዞን ወጣቶች ፌደሬሽን ፕ/ዳት ወ/ሮ መደኃኒት አየለ የበጀት ዓመቱ በዞኑ ከሚገኙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የተወጣጡ የወጣቶች ሊግ፣ ማህበርና ፌዴሬሽን አደረጃጀቶች በተደራጃና በተቀናጀ ሁኔታ የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ ተግባራት በተለያዩ መስኮች እያከናወኑ ሲሆን።
በዛሬ ዕለት በፎንቆ ከተማ አስተዳደር በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት በወጣቱ ዘንድ ትልቅ መነቃቃትን በመፍጠር በቀጣይ በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች እስከ መስከረም ወር ማጠቀለያ ድረስ እንደሚተገበር ጠቁማለች።
በዞኑ ክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባርን እውን ለማድረግ ደም በመለገስና የአቅማ ደካሞች ቤት በማደስ በአረንጓዴ አሻራ፣ በትምህርት እና በሌሎችም መስኮች ስራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ ወላጅ አጥ ህፃናትን በቁሳቁስ የመደጋፍ ሥራ ይሠራል በማለት።
በዞን ደረጃ በወጣቶች አደረጃጀት እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ 58 ሺህ 2 መቶ 70 የተለያዩ ፋይደ ያለው ችግኞች መተከል መቻሉን ገልፃለች።
በፎንቆ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለሙ አህመድ በበኩላቸው የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ግብን ለማሳካት በፎንቆ ከተማ የአረጋዊያን ቤት ግንባታ፣ የተለያዩ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ፣ የከተማ ፅዳት ዘመቻና በመኸር ወቅት ለአርሶ አደሩ የግብርና ተግባራትን የማገዝ ስራዎች መስራት መቻሉን አብራርተዋል።
በዕለቱም የዞኑ ወጣት አደረጃጀቶች በመቀናጀት በፎንቆ ከተማ ችግኝ በመትከል፣ የጎርፍ ውሃ መፍሰሻ ቦዮች ጥርጊያና ከፈተና እንዲሁም የከተማ ፅዳት ዘመቻ ተግባራት ተከናውነዋል።
በደገለ ባምቦሬ