በሆሳዕና ከተማ በአቶሚክ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በሆሳዕና ከተማ ለሚገኙ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ህፃናት ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 15/2014 ዓ.ም
የኮሌጁ ፕረዚዳንት አቶ በፍቅሩ ታስፋዬ እንደገለፁት ኮሌጁ ከጽሁፉና ከኮፒ አገልግሎት ሥራ በመነሳት በሠርተፊኬት ፣ በዲፕሎማ ፣በድግሪ ብሎም በ2ኛ ድግሪ ብቃት ባለቸው መምህራን ዘመናዊና ጥራት ያለውን ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ መሆኑንም ጠቁመው ኮሌጁ የከዚህ በፊትም ለሀገር መከላከያ በብርና በዓይነት ድጋፍ በማድረግ እንድሁም በከተማው ላይ ችግኝ መትከል፣የጽዳት ሥራና ለችግረኞች ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት
ተግባራትን እያከናወነ ያለው መሆኑን ገልፀዋል ።
አክለውም ፕሬዘዳንቱ ለውጤታማ ተግባር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ጋር ተሳስሮና ተመጋግቦ መሥራት ወሳኝ መሆኑን በመረዳት "የማህበረሰቡ አገልግሎት ቀን "በሚል መሪ ቃል ኮሌጁ ለ52 ህፃናት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ሲያበረክቱ በቀጣይነት መረዳት እንደሚችሉም ተናግረዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በርከት ታደሰ እንደገለፁት መረዳዳት ባህላችን መሆኑን ጠቅሰው ከሁሉም በላይ ህፃናት ተማሪዎችን እንዲማሩ ማበረታታት ብሩህ ዜጋን ማፍራት ነዉ ብላዋል ።
የሀዲያ ዞን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ተወካይ እና የተቋማት አቅም ግንባታ ማረጋገጫ ቡዱን መሪ አቶ ተክሉ ፊታሞ በበኩላቸው ኮሌጁ በራሱ ተነሳሽነት በመማር ማስተማር ጎን ለጎን ዛረፈ በዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በመስጠት በከተማው ከሉት የግል ኮሌጆች ግንባር ቀደም መሆኑን ጠቅሶ በከተማችን መማር ያልቻሉ ህፃናትን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ በተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅረበዋል ።
በመጨረሻም ድጋፍ የተደረገላቸው የህፃናት ቤተሰብ በሰጡት አስተያየት አሁን ያለንበት የኑሮ ሁኔታ አስቸጋሪ በሆነበት ወቅት በተደረገልን ድጋፍ መደሰታቸውን ተናግረዋል ።