31
Aug
2022
የሃዲያ ሆሳዕና ተጨዋቾች ከደጋፊዎች ጋር ትውውቅ አደረጉ
የሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ተጨዋቾችና አመራሮች ከደጋፊዎች ጋር ትውውቅ አደረጉ።
የሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ለ2015 ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የተለያዩ ተጨዋቾችን በማስፈረም ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት ተጨዋቾችንና አመራሮችን ከደጋፊው ጋር አስተዋውቋል።
በትውውቅ ፕሮግራም ላይ በርካታ ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን እንዲሁም የሃዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁ የክለቡ የበላይ ጠባቂ አብርሃም መጫና የሃዲያ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ_ፀጋዬ ተገኝተዋል።
ምንጭ:-ሆሳዕና ስፖርት