የሆሳዕና ማረሚያ ተቋም ቀደም ሲል ሲገለገልበት የነበረውን ቦታ ለዘመናዊ መናኸሪያ ግንባታ እንዲውል በተወሰነው መሠረት ለከተማው አስተዳደር አስረከበ።

የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 3/2014 ዓ.ም

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሆሳዕና ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር ተመስገንነ ቲርካሶ ለሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ለአቶ በየነ ሻንቆ እና ለከተማው ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ግዛቸው ጋዶሬ አስረክበዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ በየነ ሻንቆ እና የከተማው ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ግዛቸው ጋዶሬ በየበኩላቸው እንደገለጹት በከተማው የሚታየው የመናኸሪያ ጥበት ለመፍታት በተረከቡት ቦታ ላይ ጥምር የትራንስፖርት ማህበራትና ህብረተሰቡን በማስተባበር የዘመናዊ መናኸሪያ ግንባታ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀዲያ ጥምር የትራንስፖርት ማህበራትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

Share this Post