አሸባሪው ህውሃት ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተው ጦርነት ለሰላም ምንም ቦታ እንደሌለው ያሳየ ነው የሀዲያ ዞን ወጣቶች

አሸባሪው ህውሃት ለሶስተኛ ጊዜ የከፈተው ጦርነት ለሰላም ምንም ቦታ እንደሌለው ያሳየ ነው የሀዲያ ዞን ወጣቶች

ነሐሴ 24/2014አሸባሪው ህውሃት

ወጣቶቹ በሀገር ህልውና ጉዳይ አንደራደርም፤ ሀገርን ለማፍረስ የተቃጣውን ጠላት አስፈላጊውን ሁሉ መስዕዋትነት በመክፈል እንመክተዋለን ብለዋል።

የሀዲያ ዞን ወጣቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

ወጣቶቹ "በሀገር ህልውና ጉዳይ አንደራደርም ከቀደምት አባቶቻችንና አያቶቻችን ሀገራችን ከወራሪዎች ታድገው በክብር አስረክበውናል፣ እኛም በኛ ዘመን ሀገርን ለማፍረስ የተቃጣውን የውስጥና የዉጭ ኃይል ከአባቶቻችን በተማርነው የሀገር ፍቅርና የአሸናፊነት ወኔ እንመክተዋለን፣

ለዚህም በአስፈላጊ ነገር ሁሉ ከመንግስታችን ጎን ለመቆም ዝግጁ ነን" ብለዋል።

መንግስት ጦርነቱን ለመመከት የራሱ የሆነ ስልት ቀይሶና ህብረተሰቡን አሳትፎ የሚያደርገው ሀገርን የማዳን ጥረት እንዲያጠናክርና ለዜጎች ተጨባጭ መረጃዎችን የማድረሱን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ከመረጃ ስርዓት አንጻር የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ እኛ ወጣቶች መጠንቀቅና ሌሎችንም የማስጠንቀቅ ሥራ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመድረኩ ተገኝተዉ ወጣቶቹን ያወያዩት የሀዲያ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ኢያሱ ሻንቆ እንዳሉት አሸባሪው ህውሃት ኢትዮጵያን ለማፍረስ አስቀድሞ ኢትዮጵያዊነትን ማፍረስ ነዉ የሚል አስተሳሰብ ይዞ እየሠራ ይገኛል።

ይሁንና አሸባሪው ህውሃት መንግስት በነበረበት ዘመን የፈፀማቸዉን ወንጀሎች ሁሉ ይቅር በማለት የለዉጡ መንግስት እጁን ለሰላም ዘርግቶ የሰጣዉን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል።

ጦርነትን አማጭ አድርጎ የሚንቀሳቀሰዉ ወያኔ እኔ የማልመራት ኢትዮጵያ አታስፈልግም በማለት በመንግስት የተጀመረ ተስፋ ሰጪ የልማት ጉዞን ለማደናቀፍ የሚችለዉን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዉጭና ከዉስጥ የተወጣጡ ኃይሎች እየደገሱብን ያለዉን የግፍ ጦርነት ለመመከት ወጣቱ በሁሉም መስክ ማይተካ ሚናውን መጫወት እንዳለበት አሳስበዋል።

የዞኑ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ ወጣት ቤተልሔም አሰፋ በበኩልዋ ለሀገር መከታና ጋሻ ከማንም በላይ ወጣቱ እንደሆነ ተናግራለች።

ወጣቱ አምና በተካሄደው የህልዉና ጦርነት ወቅት ደም በመለገስ ጦርነቱን የሚቃወሙ ሰልፎች በማድረግ አልፎም ግንባር ድረስ ሄዶ ጠላትን በመፋለም የሀገር አለኝታነቱን ማስመስከሩን እንደማሳያ አንስተዋል።

አሁንም ቢሆን በፀረ ኢትዮጵያ በሆነዉ ወያኔ የከፈታብንን ጦርነት ለመመከት ወጣቱ የተለመደውን የግንባር ቀደምትነት ሚናዉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የሀዲያ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

Share this Post