በሆሳዕና ከተማ በአራዳ ቀበሌ አስተዳደር በአንዳንድ የሴቶች የልማት ቡድኖች ቁጠባን ባህል በማድረግ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እንደሚሠራ የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ገለፀ።

በሆሳዕና ከተማ በአራዳ ቀበሌ አስተዳደር በአንዳንድ የሴቶች የልማት ቡድኖች ቁጠባን ባህል በማድረግ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እንደሚሠራ የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ገለፀ።

የከ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት 06/01/2015 ዓ.ም

በቀበሌው ዎጪታ የሴቶች የልማት ቡድን ያሆዴ መስቀላ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎንዮሽ ቁጠባ 153ሺ 850 ብር እና 30 ኪሎ ግራም ቡና ለአባላቱ አከፋፍሏል ።

የከተማው እሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት በቀበሌው በቡድን የተደራጁ ሴቶች ቁጠባን ባህል በማድረግ ከልማት ቡድን ወደ ህብረት ሥራ ማህበር የተሸጋገሩበት መልካም ተሞክሮ ለማስፋት ጥረት ይደረጋል ።

የአራዳ ቀበሌ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብዙነሽ ብርቄ በበኩላቸው በቀበሌው 2014 ዓ.ም ውጤታማ ከሆኑ የሴቶች ልማት በድኖች መካከል ዎጪታና ተስፋ የሴቶች የልማት ቡድኖች እንደሚገኙበት ጠቁመው ቡድኖቹ ከጎንዮሽ ቁጠባ በተጨማሪ ወደ አራዳ ለለውጥ ህብረት ሥራ ማህበር በመሸጋገር ከ87ሺ ብር በላይ መቆጠብ መቻላቸውን ተናግረዋል ።

 

Share this Post