የ"ያሆዴ" በዓል ምንነት

የ"ያሆዴ" በዓል ምንነት

የዚህም ማሳያ የ"ያሆዴ" በዓል ነዉ፡፡ በዚህም አሮጌዉን ዓመት ሸኝተዉ አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት ነዉ፡፡

ታዲያ ይህ የ"ያሆዴ" በዓል ሲነሳ ሁሌም አብሮ የሚነሳው ያሆዴ ጭፈራ (ጨዋታ) ነው፡፡

ጭፈራውን ወጣት ወንዶች በአካባቢያቸው ተሰብስበው በየነፈራውና በየቤቱ እየተዘዋወሩ ምሽቱን ሙሉ የሚጨፍሩት (የሚጫወቱት) ጨዋታ ነው፡፡

ያሆዴ ጭፈራን ከሌሎች ጭፈራዎች የተለየ የሚያደርገው ልጆች ወላጆቻቸውን የሚመርቁበት በመሆኑ ነው፡፡

በየገቡበት ቤት ሁሉ አተካና እና ለበዓሉ ተብሎ የተዘጋጁ ምግቦችን እየበሉ የቤቱን አባወራንና እማወራ ይመርቃሉ፡፡

ያሆዴ ወጣት ልጆች ተሰብስበው "ከግብይቱ መስክ ከገበያ፣ ከየምንጩ ፣ ከየአበባው" ከየቦታው ለትንሹ ትልቁ ሲናገር፣ ባይናገር እንኳ ሲያናግር አሁን በይፋ ተበሰረ፣ጓዳ ሞላ፣ ጠቀለለ እንኳን ደስ አላችሁ! በማለት እያዜሙ በየመንደሩ አባወራ ቤት እየተዘዋወሩ የሚጨፍሩት ባህላዊ ጨዋታ እንደሆነ ከያሆዴ መጽሔት 2007 ዓ.ም ዕትም ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

 

Share this Post