ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ ዕውቅና ተቀበሉ

መስከረም 04 2015 (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ ዕውቅና ተቀበሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ያካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ ነው ብለዋል።

እንደ ሀገር ዘርፉን አካታች ለማድረግ ስለ ተጓዝናቸው ምዕራፎች ይህንን ሽልማት በመቀበሌ ክብር ይሰማኛል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ጅቡቲ ከተማ መግባታቸው ይታወሳል።

ጂቡቲ ሲደርሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።(ኢዜአ)

Share this Post